የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ ዘሪሁን ሙላቱ የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች በዱቤ ግዥና ኪራይ ውል ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሠረት የኪራይ ከፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ ለማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የንብረቱ ዝርዝር |
ብዛት በቁጥር |
የጨረታው መነሻ ዋጋ |
የንብረቱ ሁኔታ |
የጨረታው ሁኔታ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Baking Rotary Oven with Burner Brand: ALTUNTOP, Model: ATDF-250, Trolley capacity 16shelves, Origin: Turkey |
1 |
9,792,345.08
|
አዲስ
|
ዝግ ጨረታ
|
ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
|
|
2 |
Mixer Brand: ALTUNTOP, Model: ATSM120, Flour capacity-75Kg, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
3 |
Dough Divider Brand: ALTUNTOP, Model-ATK60T, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
4 |
Dough Moulder Machine Brand: ALTUNTOP, Model: ATF2, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
5 |
Proofer with Steam Generator Brand: ALTUNTOP, Model:ATPC,Origin: Turkey |
1 |
||||
|
6 |
Trolley with 16 tray Brand: ALTUNTOP Pan Dimension - 80x100 Number of pans per trolley-16 Material - Aluminum |
1 |
||||
|
7 |
Bread Slicer Brand: ALTUNTOP, Model: ATED, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
8 |
Sound Proof Generator Brand: AKSA, Model: AP33, Rated power: 30KVA |
1 |
|
|
ጨረታው መመሪያ
- በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻውን በመጥቀስ፣የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር1,958,469.02 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስምንት ሺ እራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ የያዘ በኢት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪከት ስም የተዘጋጀና በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻውን ማስገባት ይችላል።
2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፣ መናኸሪያ ከ ከተማ፣ጉዊ ቀበሌ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃጨርቅ አ/ማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው።
3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፣
3.1 የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ የታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
3.2 ገዢው ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ይጠበቅበታል ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን የጉሙሩክ ቀረጥና ታክስ የመክፈል ግዴታ አለበት።
4. የጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል።
5. ንብረቱን በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል።
6. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠሊያ ኪራይ ፣የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት።
7. የካፒታል ዕቃ ካለበት መጋዘን ወደሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣መትከያ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ተከራይ ይሸፍናል።
8. ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ቢሮ ውስጥ ይደረጋል።
9. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
10. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል፣
11. የባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 1/5ኛ (20%)
- Published: May 24, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.