በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የግረዋ ወረዳ የገንዘብ ጽህፈት ቤት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኢኒስታለሽን ስራ እንዲሁም ፈርኒቸር እቃዎች እና ለመገጣጠም ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
W/M/A/Gurawaa-2018-002

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የግረዋ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ ቤት የወረዳው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኢኒስታለሽን ስራ እንዲሁም ፈርኒቸር እቃዎች እና ለመጣጠም ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ዕቃዎቹን ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ ያደሰ መሆን አለበት።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታው ማስከበሪያ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሠርቶ ማቅረብ የሚቸል።

5. ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስና ወንጀል እና ኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን አለባቸው።

6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋቸው ዕቃዎች በተባለበት ቦታ ማድረስ የሚችልና ያሸነፋቸው ዕቃዎች በሚፈለገው መጠን ያለው መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በምስ/ሐ/ መስ/የግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

10. እቃዎች በኢትዮጵያ ማቴሪያል እስታንዳርድ የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው፡፡ በዚህ ያልተረጋገጠ እቃ ካላቀረቡ መ/ቤቱ እንደማይቀበል ማወቅ አለባቸው።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 39 90 21 53 በስራ ሰአት ደውለው ወይም በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በምስራቅ ሐረርጌ መስተዳድር የግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-10 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: East Hararge Zone Gerawa Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published: May 25, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T07:02:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders