የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ህጋዊ ካልሆኑ ነጋዴዎች የተወረሱ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ አሻንጉሊት እና ወንበሮች በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ህጋዊ ካልሆኑ ነጋዴዎች የተወረሱ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ አሻጉሊት እና ወንበሮች በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. የጨረታ ግምታዊ መነሻ ዋጋ 230,175/ሁለት መቶ ሰላሳ ሺ አንድ መቶ ሰባ አምስት ብር በሐራጅ ይሸጣል።
2. ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ ቆይቶ በ5ኛው ቀን የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግቦ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
3. የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የመሰብሰበያ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ንብረቱን ለመግዛት ተጫራቾች ከጫረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተቋሙ በሚመርጣቸው ሶስት የስራ ቀናት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ግቢ ውስጥ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት እስቶር መጥተው መጎበኘት ይችላሉ።
4. እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/አስር ሺህ ብር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ፅ/ቤት አሰርተው ማስያዝ ይኖርቦታል።
5. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታው ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት አካውንት በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ሙሉ ገንዘቡ በሁለት ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
6. የጨረታ አሸነፊ ግለሰብ ጨረታው ከአሸነፈ በኃላ የአሸነፈባቸው ንብረቶች በሁለት የስራ ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማንሳት አለባቸው
7. ከላይ በተጠቀሰው ሁለት ቀናት ውስጥ ንብረቱ አጠናቆ ያልወሰደ ተጫራች የጥበቃና የቦታ ክራይ በቀን 2000/ሁለት ሺህ ብር እንዲከፍል ይደረጋል
8. መስረያ ቤቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት ሣሪስ - ከሪስ ኢንጂነሪነግ ከፍ ብሎ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የፋይናንስ ጽ/ቤት
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ ቆይቶ በ5ኛው ቀን የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-01 14:00
- Bid opening (note): ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ ቆይቶ በ5ኛው ቀን የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Kalitiy Sub City Woreda 06 Administration F/E/D/B
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Published: May 25, 2026
- Posted at: 2026-05-26T07:23:16.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.