Security printing, forms and vouchers

የስልጤ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጥ የመደበኛ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የስልጤ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጥ የመደበኛ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

1. ለ2018 በጀት ዓመት የሚያገለግል የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት

2. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. 1% (ፐርሰንት) ማቅረብ አለባቸው

3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ስልማ አ/አ/ ቅ/ጽ/ቤት ከረሜላ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 እና ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ስልማ ዋና ጽ/ቤት በመቅረብ በአካል መግዛት ይችላሉ

4. ጨረታው የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 8፡30 ሳጥኑ ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

5. የጨረታ ሰነዱን 01 ኦርጂናል እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋ።

6. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 278 2974/ 011 277 2176/ 046-771-1293/291/231/199 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

የስልጤ ልማት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-10
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 8፡30
  • Bid opening: 2026-06-10 15:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 9፡00
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Silte Development Association
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (May 25, 2026)
  • Posted at: 2026-05-26T08:17:30.000Z
← Back to all tenders