የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገባቸው ላሉ ለተለያዩ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሪክና የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገባቸው ላሉ ለተለያዩ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሪክና የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ምድብ 1 ዕደ ማርቆስ አዲሱ መናኸሪያ፣ ለጎዛምን ወረዳ አስተዳደር፣ ለደ/ማርቆስ አልማ ጂ+10 ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አቅርቦት፣
  • ምድብ 2 ለደ/ማርቆስ አልማ G+10፣ ለደ/ማርቆስ አዲሱ መናህሪያ እና ለደ ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የሳኒተሪ ዕቃዎች አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 እና አዲስ አበባ 4 ኪሎ አልማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤ ሆኖም የጨረታ ፖስታው ገቢ የሚሆነው ደ/ማርቆስ ከተማ ድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ነው።

2) ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ የአንዱን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት/ ቅዳሜን ጨምሮ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት አለባችሁ።

3) ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ታሽጎ 3፡30 ሰአት ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም።

4) ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

5) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

6) አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል።

7) አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።

8) አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በየምድቡ የተዘረዘሩትን በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በማቅረብ ማስረከብ አለበት።

9) አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት።

10) ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።

11) ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ለደ/ማርቆስ በስልክ ቁጥር 09 20 51 44 07

ለአዲስ አበባ በስልክ ቁጥር 09 12 03 55 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በደ/ማርቆስ ከተማ/አስተዳደር መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት/ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-06-08 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት/ ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Menkorer Construction Enterprise
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T09:00:39.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders