በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቀጫ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በወረዳው በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ህትመት እና በወረዳችን በደብረ ብራሃን /022 ቀበሌ የቀድሚያ መማሪያ ክፍል ለማስገንባት ከህንፃ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ያለው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት እና መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር ጨ-1/4028/2018
ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቀጫ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በወረዳው በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ከተራ ከተራ ቁጥር 1 አስከ ተራ ቁጥር 2 ድረስ ያሉ ግንባታና አቅርቦቶች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት እና መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
1. በወረዳችን በደብረ ብራሃን /022 ቀበሌ የቀድሚያ መማሪያ ክፍል ለማስገንባት ከህንፃ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ችላል።
2. ህትመት
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች በዘርፋ የ2018 ዓ.ም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የግዥ መጠናቸው ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማረ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ በመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚቸሉ።
4. በፌዴራል ደረጃ ካላቸው የምስክር ወረቀት በተጨማሪ በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለሰልጣን የአጭር ግዜ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች ጨረታ በመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የግንባታውም ሆነ የአቀርቦቱ አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ሰፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የግንባታ ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር በተራ ቀጥር 2 ለተገለጸው የህትመት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
8. የግንባታው ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል ። የእቃ ግዥ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታም ሆነ አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም CPO / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤት -በመ/ሂ ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቀረብ አለባቸው።
10. ማንኛውም ተጫራቾች የህንፃ ግንባታ ስራ ፋየናሻሉን እና ቴክኒካል መረጃዎችን በተሰየ ፖስታ በማሸግ በግዥ ን/ስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የእቃ ግዥ ከ18/09/2018 አስከ 2 /10/2018 አየር ላይ የሚውል ሲሆን የእቃው ግዥ በቀን 3/10/2018 3:30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁ 5 ይከፈታል። የግንባታው ከ18/09/2018 እስከ 8/10/2018 ዓ.ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የግንባታው በቀን 9/10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ በ4፡00 ሰዓት ግዥ /ለ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል። በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ሳይ ስማቸው ፊርማቸውን ሙሉ አድራሻ፣የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ/ CPO /ወይም በጥሬ ገንዘብ (ሂ-1 በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው።
12. ተጫራቾቸ ለአሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
13. መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 በቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ህጋዊ ተወዳደሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ አይነትና የግዥ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ መሰረት የመሙላት ግዴታ አለበት።
14. አሸናፊው የአሸነፈውን ግንባታ ከሚፈለግበት ቦታ ሰርቶ የማሰረከብና ግዥውን በሚፈለግበት ሴክተር መ/ቤት በማስረከብ ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግዴታ አለበት።
15. በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቀረብ አለባቸው:: ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈሰጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 0416 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
18. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
19. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
ማሳሰቢያ፡-
- ባለ ህንጻ ግንባታ በማሰራት በህንፃ ተቋራ /BC/ ከሆነ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያለው በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ/GC/ ከሆነ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የምታሟሉ ተጫራቾች ሰነድ በመግዛት የወሰዳችሁ ጨረታው የሚከፈተው በ16/09/2018 ዓ.ም መሆኑ መገለፁ ይታወቃል ሆኖም በአሰራር ላይ በቀረቡ ቅሬታዎች መልስ ለመስጠት ስላስፈለገ የጨረታ መክፈቻውን ቀን 6 የስራ ቀን በመጨመር ያራዘምን ሲሆን ጨረታው የሚከፈተበት ቀን 25/09/2018 ዓ.ም 3:30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቀጫ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-16 10:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቀጫ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
- Bid bond: 1%
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: May 26, 2026
- Posted at: 2026-05-26T09:25:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.