አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ በ2017/2018 የምርት ዘመን ያመረተውን ኪንግ በርድ ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የሽያጭ መለያ ቁጥር 03/01/2018 ዓ.ም

አጋርፋ የግብርና ቴከኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ በ2017/2018 የምርት ዘመን ያመረተውን ኪንግ በርድ ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች እና ግዲታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችሳሱ።

  1. ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የእድሳት ጊዜው ያላለፈበት የሥራ ንግድ ፍቃድ።
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት, ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት የስንዴ ምርት የሰጠውን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የዋስትና ጊዜው ከ2 (ሁለት) ወር ያላነሰ የባንከ ዋስትና /CPO/ BID BOND/ በኮሌጁ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ የትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸለት በ5 (አምስት ) ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ካልፈጸመ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል።
  5. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ከአጋርፋ ግቴሙትሥ ኮሌጅ ከግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ እና አዲስ አበባ ሀይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ሀንጻ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አላጌ ማ/ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሰራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይቻላል። እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጂናሉንና ኮፒውን በመለየት አስፈላጊ ከሆነ ከተያያዥ የጨረታ ሰነዶች ጋር በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው አድራሻ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  7. የጨረታው መዝጊያ ቀን እና የሚከፈትበት ቀን በተጨማሪ በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ሲሆን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽቤት ውስጥ ይከፈታል።
  8. የጨረታው መከፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ ሆኖ በህዝባዊ ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
  9. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም አይቻልም።
  10. የምርቱን ናሙና ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባሌ አጋርፋ የግብርና ቴ/ሙ/ት/ሥ ኮሌጅ አጋርፋ ቀርበው ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በኮሌጁ እህል መጋዘን ማየት ይችላሉ።
  11. ኮሌጁ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 662 5004 አዲስ አበባ ወይም 09 11 49 08 70 / 09 30 10 80 07 እና 09 22 31 92 74 አጋርፋ የግ/ቴ /ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአጋርፋ የግብርና ቴክኒከና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና የሚከፈትበት ቀን በተጨማሪ በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ሲሆን
  • Bid opening: 2026-06-09 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና የሚከፈትበት ቀን በተጨማሪ በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ሲሆን
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T09:35:29.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders