ሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የተሰማራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ሰነዱ ላይ በቀረበው መስፈርት መሰረት መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የተሸከርካሪዎች ግዢ ጨረታ
ሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የተሰማራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ሰነዱ ላይ በቀረበው መስፈርት መሰረት መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ሀዋሳ ከተማ ፒያሳ በሚገኘው ሀዋሳ ሀይቅ የገበያ ማዕከል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዤጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ መውሰድ ይቻላል።
2. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ ቲን፤ ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ _ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ላገባው ዋጋ 10 ፐርሰንት ካቀረበው የጨረታ ዋጋ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ10 ቀናት የጨረታ ዋጋ በመሙላትና ሲፒኦ 10 ፐርሰንት በማያያዝ ካቀረቡ በኋላ ጨረታው በ10ኛው ቀን (29/09/2018 ዓ.ም.) ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 5፡15 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
6. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብት አለው።
አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ ፒያሳ በሚገኘው ሀዋሳ ሀይቅ የገበያ ማዕከል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410
ማሳሰቢያ፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 24 09 80 ወይም 09 30 06 94 87 ይጠቀሙ።
ተጫራቾች ሙሉ አድራሻና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
ሪሰረክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-06
- Publishing entity: Resurrection and Life Development Organization
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 28, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.