በአራዳ ክ/ከተማ የራስ እምሩ ጤና ጣቢያ በ 2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ቋሚ የላብራቶሪ ዕቃ እና የላብራቶሪ ግብዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/ቁ/02/2018
በአራዳ ክ/ከተማ የራስ እምሩ ጤና ጣቢያ በ 2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ቋሚ የላብራቶሪ ዕቃ እና የላብራቶሪ ግብዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን 400.00 (አራት መቶ ብር) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት በራስ እምሩ ጤና ጣቢያ ረዳት ፋይናንስ ክፍል 4ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
3. በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው በስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ እምሩ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 411 ባሉበት ይከፈታል ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል።
4. ከገዙት ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት።
6. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያስገቡ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝሩን እና ህጋዊ ማስረጃዎቹን የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ሲያስገቡ በታሸገ ፖስታ ውስጥ መሆን አለበት።
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች በተጫረቱበት ዕቃ ናሙና የማቅረብና ስፔሲፊኬሽን ለሚያስፈልገው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
9. ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረቶች ወደ 4ተኛ ፎቅ ላይ ንብረት ክፍል ማስገባበት ግዴታ አለባቸው።
አድራሻ ፡- ጎጃም በረንዳ ዝቅ ብሎ በሲመንስ በኩል አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ በተለምዶ አባኮራን ሰፈር/ በግ ተራ
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 011 126-6712
በአራዳ ክ/ከተማ ራስ እምሩ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው በስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-08 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው በስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ras Emeru Health Post
- Buyer address: ጎጃም በረንዳ ዝቅ ብሎ በሲመንስ በኩል አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ በተለምዶ አባኮራን ሰፈር/በግ ተራ
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: May 28, 2026
- Posted at: 2026-05-28T09:02:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.