የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር የቁም ባህር ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ቁጥር ኢቅባማ/ግጨ-01/2018 የቁም

የጨር ዛፍ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ከማያስተዳድራቸው በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ ከሚገኝ ቦታዎች ጠቅላላ የባህር ዛፍ መጠን 2330ሜ3 (በሜትር ኩብ) ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የቁም ባህር ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ይህ ለተለያየ አገልግሎት የሚውል የቁም ባህር ዛፎች በእንጦጦ ይገኛሉ።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ቢሮ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺ) ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ከጠዋቱ 3፡ዐዐ-6፡3ዐ እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡3ዐ -11፡3ዐ ይሆናል።
  3. ተጫራቾች ለሚገዙት የዛፍ መጠን የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 1ዐ% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ሥም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ነገር ግን በተጠየቀው መሠረት ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድድር ውጪ ይደረጋል።
  4. ተጫራቾች ለሚገዙት የዛፍ መጠን የመግዣ ዋጋ በተያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ከታች በተገለጸው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  7.  አሸናፊ ተጫራች (ቾች) የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከማሕበሩ ጋር ውል መፈራረም አለበት/አለባቸው/ ክፍያው ከተፈጸመ ጀምሮ ለዛፍ ቆረጣው በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ባህርዛፉን ማንሳት አለበት/አለባቸው/።
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውል እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ይሁን እንጅ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) የሚዘጋቸው በአላት ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ከተፈለገው ሥራ ጋር ተዛማጅነት ያለው እና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች /ቾች/ አሸናፊነቱ /ታቸው/ ተገልፆለት/ላቸው/ ውል በገባ /በገቡበት/ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን/ያሸነፉበትን/ ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርበታል /ይኖርባቸዋል/። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ገቢ ይደረጋል።
  11. አሸናፊው ተጫራች በመንግሥት አዋጅ መሠረት የተጣለውን የሽያጭ ታክስ ሮያሊቲ ክፍያ በመንግሥት አስራር መሠረት ለማሕበሩ የመከፈል ግዴታ አለበት።
  12. የቁም ዛፉን ቆርጦ ለማንሳት የተፈቀደው 30 (ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል።
  13. ማሕበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በቦሌ መንገድ፣ ከቦሌ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት ከሚገኘው

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ ጀርባ፣ በቀድሞው ራስ

ከበደ መንገሻ ቅርስ ቤት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ጽ/ቤት።

የቢሮ ስልክ ቁጥር ፡ 011 515 8802

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውል እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-06 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውል እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Heritage Trust (EHT)
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ፣ ከቦሌ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ በስተጀርባ፣ ከኢዮብ የድግስ ዕቃዎች ማከራያና የድንኳን ሥራ በስተቀኝ በኩል፣ በቀድሞ የራስ ከበደ መንገሻ ቤት - ቢሮ ቁጥር 2
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 2,000.00 ብር
  • Published: May 27, 2026
  • Posted at: 2026-05-28T09:24:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders