በደ/ኢ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን የሣላማጎ ወረዳ ፋይናንስ /ጽ/ቤት የሴቶች የንጽህና መጠበቅያ ክፍል /MHM/ እና የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ /incinerator/በግልጽ ጨረታ የግዥ ዜዴ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ግዥ ፈፃሚ ጽ/ቤት የሳላመጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት - የግዥው መለያ ቁጥር_ግልጽ ጨረታ ዋን ዋስ (ግ/ጨ/ዋ/ዋ) 03/2018
በደ/ኢ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን የሣላማጎ ወረዳ ፋይናንስ /ጽ/ቤት በብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም በተመደበ በጀት ለወረዳው ትም/ት/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መደበኛ ትም/ት ቤቶች ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተገለጹትን የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ህጋዊ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዜዴ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
አሰሪ መ/ቤት |
ጥቅል የጨረታ ቁጥር |
ሎት |
የሚሰራው ስራ/ፕሮጀከት/ |
ስራው የሚሰራበት ቦታ |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር መጠን |
|
1 |
ትም/ት ጽ/ቤት |
_ |
_ |
የሴቶች የንጽህና መጠበቅያ ክፍል /MHM |
በሃና አንደኛና መካከለኛ የመ/ደ/ት/ቤት |
20.000
|
|
_ |
የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ /lncinenator/ |
በሃና አንደኛና መካከለኛ የመ/ደ/ት/ቤት |
10,000
|
በዚህም መሰረት ፡-
1. ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆነ ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጭ ማህበር ብቻ
2. በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስተር ወይም በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተመዝግቦ ለ2018 በጀት ዓመት ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው ደረጃ መሰረት የታደስ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትከፈት ማቅረብ የሚችል፣
3. ለ2018 የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣
4. የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
5. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
6. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
7 የግብር ግዴታቸውን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ለ208 በጀት ዓመት በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታክስ ክሊራንስ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን / መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታውቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 አስር / ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሣ/ማ/ወ/ ገቢዎች ጽ/ቤት ቀርባችሁ የማይመለስ ብር 400/ አራት መቶ ብር / ብቻ በመክፈል እና ህጋዊ ደረሰኝ በመቀበል የጨረታ ሰነዱን በሣ/ማ/ወ/ፋ/ስ /ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 08 በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን። ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሰነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተደርጎ እና ተዘጋጅቶ ቴክኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ 1 እንዲሁም ፋይናሻሉ ላይ ፋይናሻል ኦርጂናል እና ፋይናሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ለዚህ ጨረታ ስራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ልክ ከጠዋቱ 3፡30- 6፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት ሰነዱ መግባት ይኖርበታል። ጨረታው በዕለቱ 6፡01 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደ/ኢ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን የሣ/ማ/ወ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 12:01
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 6፡01 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-08 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 8:30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: South Omo Zone Salamago Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T09:37:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.