በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለቶጎ ጫሌ መገንጠያ -ጅጅጋ ኤርፖርት የአስፋልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ለአማካሪ ድርጅቱ ሰራተኞች ለፕሮጀክቱ ስራ እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚውል በቁጥር (4) አራት ዳብልካፕ ተሽከርካሪ መከራየት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የቀላል ተሽከርካሪ ኪራይ

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለቶጎ ጫሌ መገንጠያ -ጅጅጋ ኤርፖርት የአስፋልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ለአማካሪ ድርጅቱ ሰራተኞች ለፕሮጀክቱ ስራ እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚውል በቁጥር (4) አራት ዳብልካፕ ተሽከርካሪ መከራየት ይፈልጋል።

ስለሆነም አከራዮች የሚያቀርቡት ዳብል ካፕ ተሽከርካሪ የስሪት ጊዜው እ.ኤ.አ ከ2010 ጀምሮ እንዲሁም የፈረስ ጉልበታቸው ከ2800cc ጀምሮ (በላይ) የሆነ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት፣

3. የባለቤትነት መታወቂያ ሊብሬ የሚያቀርብ፣

4. የ3ኛ ወገን መድን ሽፋን የተገባለት፣

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በፖስታ አድርጎ በማሸግ ተሽከርካሪው በቀን የሚከራይበትን ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተገለፀው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሠረት ግልጽ በሆነ መልኩ ማቅረብ አለባቸው።

7. ነዳጅ እንዲሁም የጥገና፣ የሹፌር ደመወዝና አበል በአከራይ ይሸፈናል።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322267979(የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ብር 300፡00 (ሶስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።

9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

11. አሸናፊ ተጫራቾች አጠቃላይ የቴክኒክ ምርመራውን ካለፈ ውል በመፈፀም ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት አለባቸው።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +025 111 1313 / 09 29 06 32 49 / 09-67-47-44-90 / 09 27 63 61 26 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-13
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-13 11:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 27, 2026
  • Posted at: 2026-05-28T10:40:32.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders