ኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአጥር ግንባታ (አዳማ ከተማ) ለመገንባት ድርጅቶች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አጥር ለመገንባት ድርጅቶች አወዳድሮ ለማሰራት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር . ኢ.ግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/16/2018
|
ተ.ቁ |
የጨረታ አይነት እና ቦታው |
ደረጃ
|
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (የማይመለስ) ብር |
የጨረታ መዝጊያ መከፈቻ ቀንና ሰዓት |
||
|
የመዝጊያና ቀን |
የመዝጊያና ሰዓት |
የመክፈቻ ሰዓት |
||||
|
1 |
የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአጥር ግንባታ (አዳማ ከተማ) |
ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይንም ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ |
500.00
|
ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00
|
4:30
|
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በዝርዝር እንደተገለፀው እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካልና ፋይናንሽያል መስፈርት መሰረት ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ
የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ደረጃቸው ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ እንደተገለፀው ሆኖ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ቲን ፤ ቫት በEGP የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባችሁ እና ከኮንስትራክሽን ሚኒስተር የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ ኤማ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ከፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለፀው ብር መሰረት በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ብቻ በግልፅ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና (ለ60 ቀናት የሚቆይ) ማስከበሪያ ብር 60 ሺህ (ስልሣ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሁኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖረሽን
+251911984467 /+251910567578 አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-11 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
- Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T10:50:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.