በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን አስተዳደር የኤሶል ልዩ 2ኛ ደ/ት/ቤት የመማሪያ ክፍልና ላቦራቶሪ ግንባታን፣ በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን አስተዳደር የኤሶል ልዩ 2ኛ ደ/ት/ቤት የመማሪያ ክፍልና ላቦራቶሪ ግንባታን፣ በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት -
1. በፌዴራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር ወይም በክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ ደረጃ 5(አምስት) እና በላይ የሆነ ጠቅላላ/ህንጻ/ ስራ ተቋራጭ
2. በፌዴራል ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ ለ2018 ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው ደረጃ መሰረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
5. የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታክስ ኪሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ
6. በፌዴራል ወይም በክልሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፤
7. ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራ ውሎች በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረክብ ለመሆኑ፣ የግንባታ ጥራት ማጓደል፣ ማዘግየት፣ ውል ማቋረጥ ወዘተ የውል አስተዳደርና አፈጻጸም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ማስረጃ ያለው፤ በመሆኑም ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀክቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለ በጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታዉ መሳተፍ አይችልም። ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል።
8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ የስራ ቀናት ውስጥ ከአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው በመሳተፍ መወዳደር ይችላል።
9. ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን፤ አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ቴክኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ እና በማሸግ/ ለዚሀ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሃያ ሁለተኛው /22ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል። ጨረታው በዚሁ ዕለት 6.30 ሰአት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርአትም በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ፋይናንሽያል ዶክመንት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር የቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251-91 613-5977 ወይም +251-92 610-4134 በመደወል መረዳት ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-20
- Bid closing time: 12:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ ሁለተኛው /22ኛው ቀን (የሥራ ቀን) 6.30 ሰአት
- Bid opening: 2026-06-20 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ ሁለተኛው /22ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: በደ/ኢ/ክልል አሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T10:52:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.