የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሼድ ጥገና ሥራ
የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሲዳማ ክልላዊ መንስት በይርጋለም ከተማ አስተዳደር የወጣት ሴቶችና ልጃረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ የሼድ ጥገና በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት
2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ማህበራት፣
4. ተጫራቾች ለጨረታ ካስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ከተጨ.እሴ.ታክስ ጋር 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሄልቬታስ አካውንት ወጋገን ባንክ አካውንት ቁጥር 0863033111301 በማስገባት የባንክ ገቢ ማረጋገጨ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት ።
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቢሮ (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ ) በመቅረብ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 3, 2018 (_June 10, 2026) ተከታታይ የሥራ ቀናትንና ሠዓት በመጠቀም ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል፡አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ ቲክኒካል በአጠቃላይ በአንድ ትልቅ ኤንቬሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ እና በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስክ ሰኔ 3, 2018 (_June 10, 2026) ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በሥራ ቀንና ሠዓት በሄልቬታስ- አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 8.30 ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) ይከፈታል።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0939064059/0911331955
የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሀዋሳ
Tender details
- Deadline: 2026-06-10
- Publishing entity: የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
- Published: May 27, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.