በአብክመ ሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

በአብክመ ሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድሀኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ፣የስራ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር / ' የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃዎችን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል

2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ከነቫቱ መሙላት አለባቸው

3. ተጫራቾች የሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ በማስላት ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል ያስያዙበትንም ደረሰኝ ወይም CPO ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።

4. የእያንዳንዱን መድሃኒት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሙላትዎን ያረጋግጡ፤

5. የዘርፉን ንግድ ፈቃድና የመሳሰሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክሜንት ጋር ተያይዘው በፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው

6. በፖስታው በውጪ ገፅ እና በዋጋ መሙያው የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራች ስም፣ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፤

7. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

8 በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡

9. የጨረታ ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 21/9/2018 እስከ 6/10/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፅ/ቤታችን ቢሮ ይከፈታል፣

11. ጨረታው ታሽጎ የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

12, አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ወይም በጥቅል መ/ቤቱ በሚያዋጣው መሰረት ነው፡፡

13. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፅ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዢ መመሪያው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

14. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጁ መሰረት በተከታታይ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

15. ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።

16. አሸናፊው ላቀረባቸው መድሃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ዋጋ የሚከፈለው በውሉ መሰረት መድሃኒቶችን መሳሪያዎችን ከፅ/ቤታችን መድሀኒት ቤት ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ አጠናቅቆ ገቢ ማድረጉ ሲረጋገጥ ነው።

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0116850139/0601/0913121292 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 21/9/2018 እስከ 6/10/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-15 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 21/9/2018 እስከ 6/10/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Menz Gera meder Woreda Animal and Fisheries Development Office
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: May 29, 2026
  • Posted at: 2026-05-29T07:17:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders