የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ሽ/ሪ/ግ/ጨ/06/2018
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
የዕቃው ዓይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ
|
የጨረታው መዝጊያ ቀን |
የጨረታው መክፈቻ ቀን |
|
የቢሮ ፈርኒቸር
|
60,000
|
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት። |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000482105592 EEU-ፊንፊኔ ዙርያ ዲስትሪክት በሚለው በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
5. አድራሻ፡- 22 ድንበሯ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽገር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።
6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ስፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሽገ/ሪጅ/ግ/ጨ/006/2018 የሚል በሚወዳደሩበት ሎት ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን በዚያው ቀን ሰኔ 10 2018 ዓ.ም 4፡30 ጠዋት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
8. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-011-522-6504 መደወል ይችላሉ።
10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-06-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-17 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: 60,000 ብር
- Bid document price: 400.00 (አራት መቶ ብር)
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T07:36:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.