በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የተፈጩ ጠጠሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢመአ ሻሽ/098/2018
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የተፈጩ ጠጠሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ/አ ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል።
7. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 211 4616 መጠቀም ይችላሉ።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሽመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Road Construction Corporation
- Buyer address: ዓለም ገና ቀበሌ 02 አዲስ አበባ-ጅማ መሥመር 19 ኪሜ
- Bid bond: 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር )
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T08:00:20.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.