Amharic
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔር ችሎት ኮንፕሬሰር እና ባጃጅ በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ እድሜአለም እጅጉ ተሰማ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አዳሙ መኮንን ዘሪሁን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ የፍርድ ባለዕዳ ንብረት የሆነው 1ኛ ኮንፕሬሰር በሃራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም 2ኛ የሰሌዳ ቁጥር 01-06158 ድሬ የሆነ የባጃጅ ተሽከርከካሪ በሀራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 30,413.78 /ሰላሳ ሺህ አራት መቶ አስራ ሶስት ብር 78/100/ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል።
ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡45 እስከ 4፡20 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ለኮንፕሬሰር ከጠዋቱ 4፡25 እስከ 5፡10 እንዲሁም ለባጃጁ ተሽከርካሪው ከ5፡15 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ ታዟል።
የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወይም በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ወዲያውኑ በCPO ማስያዝ አለባቸው። ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔር ችሎት
Tender details
- Deadline: 2026-06-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-13 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት
- Bid bond: 25%
- Published on: Melekite Dire (May 27, 2026)
- Posted at: 2026-05-30T06:19:47.000Z