የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በበንሳ ዳዬ ከተማ ሊያሰራ ላቀደው የG+2 የቢሮ ሕንጻ ቀሪ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በበንሳ ዳዬ ከተማ ሊያሰራ ላቀደው የG+2 የቢሮ ሕንጻ ቀሪ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት -

1. ደረጃቸው GC‐5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ የሥራ ተጫራቾች 2018 ዓ/ም ፊቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።

2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።

3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።

4. የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳከሮ ትክከለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

5. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 800,000.00 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE) ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

6 የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተቀው ማረጋገጥ አለባቸው።

8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያመሠረት ተሞልቶጨረታማስከበሪያ (bidbond / security)፣ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያዉ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።

1ዐ. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-19
  • Publishing entity: Eastern Sidama Zone Higher Court
  • Bid bond: 800,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 30, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders