የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ታጣፊ/ ሲኒማ /ወንበር መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት መለያ ቁጥር 05/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ታጣፊ / ሲኒማ / ወንበር ብዛት 2500 ( ሁለት ሺህ አምስት መቶ ) ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
1.ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
2.የተጨማሪ አሴት ታክስ ተመዝጋብቢ አና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫቾራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ cpo ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከአጠቃላይ ግዥ 1.5% የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር ብቻ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000342552424 በማስገባት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ምድር ቤት በሚገኝ ቢሮ ቁጥር 8 ቀርበው ሰነዱን ማግኘት ይቻላል።
- ለጨረታው የሚቀርበውን ሲኒማ የአዳራሽ ወንበር ይዘትና ዓይነት የሚያሳይ ፎቶ ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ ይኖርበታል።
- በተጨማሪም ጽ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈልገውን የወንበር ዓይነት በተጫራች መመሪያ ላይ ተገልጿል።
5. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ለየብቻ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ በፖስታው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ መገለጽ አለበት።
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት 9፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉበትን ዕቃ አስከ ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ በማቅረብ ገቢ በማድረግ ድጋፍ ስሚደረግላቸው ወረዳ ድረስ በማጓጓዝ ገጥሞ ያስረክባል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት በሚደረግ ወቅት ወይም አስቀድሞ የዕቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለበት።
8. ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይሆናል።
ዝርዝር የጨረታ ገዥ ሃሳብ በተጫራቾች መመሪያ ላይ ተገልጿል።
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ሀዋሳ 046-212-4290-/-91-/09 98 00 08 77
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-09
- Publishing entity: Sidama National Regional State Administration Office
- Bid bond: 1.5%
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ) ብር
- Published: May 30, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.