የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለከፍተኛ አመራሮች የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 023/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለከፍተኛ አመራሮች የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል መሆኑና ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1ኛ ፎቅ በአቅርቦት መምሪያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 156 9869
ኢሜይል procurement@press.et
አድራሻ ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Enterprise
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 31, 2026
- Posted at: 2026-06-02T07:32:47.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.