የጉምሩክ ኮሚሸን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም እስካቫተር (EXCAVATOR) ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሸን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም እስካቫተር (EXCAVATOR) ተሸከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች ከቀን 26/09/2018 ጀምሮ በማየት እና የዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፦

1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣

2. ለሐራጅ ጨረታው ለእያንዳንዱ መኪና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.አ (CPO) ማስያዝ የሚችል፣

3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ የተሽከርካሪውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ) (C.PO) ማቅረብ የሚችል፣

4. ተጫራቹ በሐራጅ ጨረታ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ ለራሱ ያቀርባል፣

5. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤

7. ተሽከርካውን አሽንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከሱ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤

8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መስረዝ ይችላል፤

10. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤

11. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሽንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤

12. ተጫራች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 26/09/2018 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው 28/09/2018 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

13. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 28/09/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

  • አሸናፊው ተጨማሪ ለሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
  • የቻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: May 31, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders