ፈያ ኢንተርግሬትድ ደቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን Emergency Water Trucking Services Including 10,000 liters Plastic Tanker supply and installation በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
BID Ref # 0024/2026
ድርጅታችን ፈያ ኢንተርግሬትድ ደቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ላለፉት 24 ዓመታት በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ከመንግስትና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን እየሰራ ያለ ህጋዊ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ-አድራጎት ድርጅት ነው:: ከ EHF በገኘነው Rapid life-saving integrated response to disease outbreaks and acute malnutrition in Oromia Region, Ethiopia. ድርጅታችን ከዚህ በታች የተገለፀውን ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የስራው አይነት |
ብዛት |
|
1 |
Emergency Water Trucking Services Including 10,000 liters Plastic Tanker supply and installation for Sewena Woreda, East Bale Zone as indicated in BOQ |
2 trucks each with 20,000 liters capacity
|
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሁሉም አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በድርጅታችን (ፈያ ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን) ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በታች ያስያዘ ከጨረታው ዉድድር ውጪ የሚደረግ ይሆናል።
3. ስለጨረታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ ሰባት (7) ቀናት ከፈያ ኢንትግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ዋናው መስሪያ ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በስም (wax) በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በቀን ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 ይከፈታል።
6. አሸናፊው ተጫራች ባሸነፈበት ዋጋ ያሸነፈበትን የእቃ ዝርዝር ውል በገባ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
7. ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብና ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸ ( ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ውጤት) በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
8. ተጫራቾች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: አልሳም የመኖርያ መንደር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር : +251 - 11 557-8114
Tender details
- Deadline: 2026-06-10
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-10 16:30
- Bid opening (note): ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Fayya Integrated Development Organization (FIDO)
- Buyer address: Nifas Silk lafto Sub - City Near to Golf Club (Old Airport, Torhailoch)
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: May 31, 2026
- Posted at: 2026-06-02T11:15:48.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.