የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ አይነት የፖሊስ ደንብ ልብስ እና የተለያዩ አይነት የሚሊተሪ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር /ሁለት/02/2018 ዓ.ም የተለያዩ
አይነት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ክልል፣ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በጀታቸውን በወቅቱ ለመያዝ እንዲረዳቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ አይነት የፖሊስ ደንብ ልብስ እና የተለያዩ አይነት የሚሊተሪ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች -
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምሥክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የትብብር ደ/ቤ ማቅረብ የሚችል፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃውን ከጠቅላላ ዋጋ 2% /CPO/ ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው የተሞላው ዋጋ ከዘጠና ቀናት (90) በታች መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የቴክኒካል ስፔስፍኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 25% የመጨመር መብት አለው።
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 0910062954 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
ሆሳዕና
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Publishing entity: Police Commission of the Government of Central Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 50.00 ብር
- Published: Jun 01, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.