በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ሲዳማ የጭሬ ወረዳ አስተዳደር/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደዉ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ሲዳማ የጭሬ ወረዳ አስተዳደር/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሲሰራ ላቀደዉ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች በሙሉ እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።

1. በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዝያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ሆነው መጸዳጃ ቤት ሥራ ላይ ከዚህ በፊት የሠሩበት የስራ ልምድ ያላቸው።

2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ መመዘግባቸውን የሚያሳይ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾቹ ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት /ቴክኒክ/ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦርጅናል/ ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክረው ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

4. የጨረታ ማስከበሪያ/bid security/ ብር 30,000 /ሳላሳ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና/bank guarantee/ ወይም የክፍያ ማዘዣ/cpo/ ከመጫራቻ ሰነድ ወይም የቴክኒካል ዶክመንት ጋር ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የሥራ ቦታ/site/ በራሳቸው ወጭ አይተው /Vist/ ማረጋገጥ አለባቸው።

6. ተጫራቾች በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፍቃዳቸው እና ተ.ዕ.ታ /VAT/ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታከለ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ19 /አስራ ዘጠኝ/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 1600/አንድ ሺህ ስድስት መቶ/ ብር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ሲ/ጭራ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ።

7. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተው ጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና /ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ /ሁለት/ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በትልቁ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁለቱም ዶኩመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጭሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለዚሁ አግልግሎት የተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያው የቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡-

1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

2. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ፡ 09 10 74 06 70 / 09 26 06 45 20

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-20 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Zone Chire Woreda FEDB
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,600.00 ብር
  • Published: Jun 01, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T11:54:22.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders