በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት በ4ኛ ሩብ ዓመት የምልምል ሰልጣኝ ወታደሮችና በሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ቀለብ፣ የግብርና ምርት ውጤቶችን፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችና የባልትና ውጤቶችን እንዲሁም የተጣራ የበሬ ስጋ እና የበቆሎ ቂንጬን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት በ4ኛ ሩብ ዓመት የምልምል ሰልጣኝ ወታደሮችና በሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ቀለብ በሎት 1 የግብርና ምርት ውጤቶችን በሎት 2 የኢንዱስትሪ ምርቶችና የባልትና ውጤቶችን እንዲሁም በሎት 3 የተጣራ የበሬ ስጋ እና የበቆሎ ቅንጨን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው

1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤

5. የዘመኑ ግብር የፈለ/ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

6. በቀለብ አቅርቦት የመልካም ስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

7. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣

8. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፤

9. ተጫራች የአንድ ዋጋ መሙላት ያለበት ያለ ቫት ሆኖ ሁሉንም ቀለቦች ዋጋ በመሙላት ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል፤

10. በጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት 1 እና በሎት 2 ላይ በተቀመጡ የቀለብ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመጣል:: በሎት 3 በተቀመጠው ዝርዝር በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመረጣል፣

11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጪ ይሆናል።

12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም ከተራ ቁጥር 1-7 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸገረ የሚወዳደርበትን ሎት በመፃፍ ማቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጪ ይሆናል።

13. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።

14. የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።

15. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በስራ ቀንና ሰዓት ከ24/09/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 04/10/2018 ዓ/ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን 05/10/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው:: በዚሁ በቀን 05/10/2018 ዓ/ም ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡

17. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በየ ሳምንቱ፣ በየ15 ቀኑ ወይም በየ ወሩ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ቀለቡን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፣ የቀለቡን ጥራት የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ከ3-5 ባሉት ቀናት ውስጥ ቀይሮ ጥራት ያለው ቀለብ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ለቀለብ አቅርቦት ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ረጅስተራር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።

19. የቀለብ አቅርቦት የውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ከ5-6 ወራት ድረስ ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የቀለብ ማዘዣ መሰረት እያቀረበ የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፣ የዋጋ ማሻሻያም አይደረግበትም፣፣

20. ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

21. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

22. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፤ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በስራ ሰዓት ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid opening: 2026-06-12 13:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Birsheleko Basic Military Training School
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 01, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T11:58:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders