የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዝብ ጽ/ቤት የኩታበር ወረዳ አስተዳዳር ም/ቤት ላስገነባው የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስታንዳርዱን የጠበቀ መቀመጫ ወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች ከደረጃ 5 /አምስት/ በላይ የሆኑ ተቋራጮች (GC-5/BC 5/RC 5 ጠቅላላ ወይም የህንጻ ተቋራጮች ግዥ መፈጸምና ለማስገጠም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዝብ ጽ/ቤት የኩታበር ወረዳ አስተዳዳር ም/ቤት ላስገነባው የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስታንዳርዱን የጠበቀ መቀመጫ ወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች ከደረጃ 5 /አምስት/ በላይ የሆኑ ተቋራጮች (GC-5/BC 5/RC 5 ጠቅላላ ወይም የህንጻ ተቋራጮች ግዥ መፈጸምና ለማስገጠም ይፈልጋል።

ስለዚህ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋራጮችና እቃ አቅራቢዎች፡-

1. የኮንትራክተር ደረጃ መስፈርት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የእቃ አቅራቢዎች ወይም ከደረጃ 5/አምስት/ እና በላይ በሆኑ ተቋራጮች (GC-5/BC5/RCS) ጠቅላላ ወይም የህንጻ ተቋራጮች የሆኑ፣

2. የሚገዛው ወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች በዲዛይኑና በሳንፕሉ መሰረት ግዥ ፈጽሞ ማቅረብ የሚችልና መግጠም የሚችል።

3. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው።

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በቴክኒካልና ፋይናሺያል በኦርጂናልና በኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዛውን የወንበርና ሌሎች በአዳራሹ ውስጥ የሚገጣጠሙ እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን ማግኘት ይቻላሉ፤

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚያቀርበው ጠቅላ ላ እቃ ዋጋ 300000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው የኢንሹራንስ ቦንድ ወይም የግል ቼክ ተቀባይነት የለውም።

8. ጽ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ድምር ነው፣

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው ሠዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ነው።

11. 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ጨረታው 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0334480228/ 0914054354/0914051585 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: South Wello Zone Kutaber Woreda FEDB
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 02, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T07:23:02.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders