በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የመማሪያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለጋዝጊብላ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለብ/ጀ/አበባው መንግስቴ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ትም/ቤት ለቅድመ አንደኛ አገልግሎት የሚውሉ የመማሪያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው እና ደረጃ 5 እና ከዛበላይ ያለው፣

2. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሙያ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው

3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ 1-3  የተዘረዘሩትን መረጃዎች መያዝ አለባቸው።

5. የሚሰራው ግንባታ የስራ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ)ብር በመክፈል በጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል :: የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰአት ብቻ መግዛት ይጠበቅባቸዋል፤

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሞሉት ጠቅላላ ዋጋው (ቫትን ጨምሮ) 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ አንድ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋናውን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ለሚፈልጉ በፖስታ አሽገው የጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጋ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 50 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን እስከ 22ኛ ቀን ከጧቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ እለት ከጠዋቱ 3፡31 ይታሸግና በዛው እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፤ ይሁን እንጅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው።

9.የግንባታ ስራው ተጠናቆ ርክክብ ከተፈፀመበት ጀምሮ ለ1 ዓመት የሚሆን 5% ሪቴንሽን የሚያዝ ይሆናል።

10. በጨረታው 1ኛ የወጣው ተጫራች ውል እስኪወስድ ድረስ 1ኛና 2ኛ የወጡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስላቸውም፤ ሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ግን አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ መውሰድ ይችላሉ።

11. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር (ዝግ ከሆነ) በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

12. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል።

13. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

14. በጨረታው ለመሳተፍ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 09 21 26 48 53 ወይም 09 21 19 21 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡31
  • Bid opening: 2026-06-23 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Gazgibila Woreda FEDB
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 02, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T08:20:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders