የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ በ14/2018 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ዘርፍ |
የጨረታው ዓይነት |
ዕቃው ያለበት ቦታ |
|
1 |
የፅዳት ዕቃዎች |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
2 |
ፕላስቲክስ ሸራ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
3 |
አልባሳት |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
4 |
ጫማ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
5 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
6 |
የባጃጅ ጎማ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
7 |
ኮስሞቲክስ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
8 |
መለዋዎጫ |
ግልፅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
9 |
ጫማ |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
10 |
ፓኪንግ ማሽን |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
11 |
የኮስሞቲክስ ዕቃዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
12 |
ፈሳሽ ኬሚካል |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
13 |
ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና መገናኛ መሳሪያዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
14 |
ያገለገሉ የቤት ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም ። በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል።
2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00- 5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ኮስሞቲክስ ዕቃዎች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ)፤ ጫማ (ምድብ 01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ)፤ ጫማ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ)፤ ፈሳሽ ኬሚካል ብር 50,000 (አምሳ ሺ ብር)፤ ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና መገናኛ መሳሪያዎች (ምድብ 01) 100,000 (አንድ መቶ ሺ)፤ (ምድብ 02) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር)፤ ያገለገሉ ያገለገሉ የቤት ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች (ምድብ 01) ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፤(ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው ዓይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 02/10/2018 |
ዐ3/10/2018 ዓ/ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል |
|
2 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 02/10/2018 |
03/10/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
5. ጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የዕቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም ዕቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. የዕቃውን ናሙና (sample) ሳያይ የሚጫረት ተጫራች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑ ይታወቅ።
11. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።
12. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡- 0332401510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-10
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-10 10:00
- Bid opening (note): የጨረታው ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Afar
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Jun 03, 2026
- Posted at: 2026-06-03T08:40:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.