የአክሲዮኖች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍባለመብት እነ ወ/ሮ ሂሩት ዩሀንስ (2 ሰዎች ) እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ግዛው አንዳርጌ (2 ሰዎች)መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 300741 በ13/5/2017 ዓ.ም እና በመ/ቁ 335371 በ25/7/2017 ዓ.ም በመ/ቁ 335371 በ26/9/2017 ዓ.ም በመ/ቁ 335371 በ21/05/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በፍርድ ባረፈበት በፍ/ባለዕዳ በአቶ ወንደሰን በቀለ ተሰማ ስም በአዋሽ ባንክ ተመዝግቦ የሚገኝው የተከፈለ 218 አክሲዮኖች የእያንዳንዳቸው ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 218,000 (ሁለት መቶ አስራ ስምንት ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት ከጨረታው በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-07-02 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 02, 2026
- Posted at: 2026-06-03T09:00:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.