የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዉተሮች፣ ፐሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የተለያዩ የዉሃ እቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ዕቃዎችን ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ሠመራ/ስተአ/002/2018
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዉተሮች፣ ፐሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የተለያዩ የዉሃ እቃዎች፣የግንባታ እቃዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በድጋሚ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሠመራ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከግንቦት 25 /2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 08 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የከፍያ ማዘዣ / CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3) ማንኛውም ተጫራች ከግንቦት 25 /2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 08 /2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ሠመራ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት/መጎብኘት ይችላል።
4) ጨረታው ሠመራ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሰኔ 08 ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዕለቱ ሰኔ 08 ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
6) ተጨራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +2519-23-96-64-45 ፣ 2519-66-01-66-56 ወይም 2519-13-22-86-35 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሠመራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-06-15 15:00
- Region: Afar
- Publishing entity: የስደተኞችና ተመላሾች አገልገሎት ሰመራ ቅ/ጽ/ቤት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 02, 2026
- Posted at: 2026-06-03T09:20:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.