ኤረር የገበሬዎች ኃ/የተወሰነ ህብረት ሥራ ዩኒየን በቢሾፍቱ ከተማ ኢንቨስትመንቶችን ቢዝነስ ፕላን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኤረር የገበሬዎች ኃ/የተወሰነ ህብረት ሥራ ዩኒየን በቢሾፍቱ ከተማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ኢንቨስትመንቶችን ቢዝነስ ፕላን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
- የጤና ፋብሪካ
- የዶሮ እርባታ
- የከብት እርባታ
- ነዳጅ ማደያ
- የድርጅቱን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን ለማሰራት ማሟላት ያለባቸው
1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የሥራ ፍቃድ እና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈለ ፣
2. ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብይኖርባቸዋል።
3 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታ ካቀረቡት ዋጋ (5%) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፣
4. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታ ሰነድ በግልፅ ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000769553 ብር 600 በመክፈል ከኤረር የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ደረሰኝ መውሰድ ይቻላል።
7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በዚሁ እለት በ8፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል ነገር ግን ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከዩኒየኑ የስብሰባ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል።
8. ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኤረር የገበሬዎች ኃ.የተወሰነ የህብረት ሥራ ዩኒየን
ቢሾፍቱ
Tender details
- Deadline: 2026-06-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-20 14:15
- Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Errer Farmers' Cooperative Union
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 600.00 ብር
- Published: Jun 03, 2026
- Posted at: 2026-06-03T09:29:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.