በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳዳር የደሀና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በትምህርት ጽ/ቤት በጀት ለ012 ሲልዳ ቀበሌ የመዋለ ህጻናት ት/ቤት ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 04/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳዳር የደሀና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በትምህርት ጽ/ቤት በጀት ለ012 ሲልዳ ቀበሌ የመዋለ ህጻናት ት/ቤት ግንባታ፤ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2. የተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት፤

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ያላቸው፤

4. ከደረጃ 7 በላይ /GC. BC/

5. በየትም ቦታ አሸናፊ ሁኖ፤ውል ወስዶ እንደ ውሉን ያጠናቀቀ ፤እና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፤

6. ሲቪል መሃንዲስ ያለው፤

7. ያለ ቅድመ ክፍያ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ 300,000/ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ/ ከመ/ቤታችን ገ/ያዥ ገቢ በማድረግና ፤ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

9. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ (ከገበያው ወይም ከመሃንዲሱ ግምት 25 ፐርሰንት) ዝቅ ብሎ ያቀረበ ድርጅት ወይም ተቋራጭ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ (cost break down) የግንባታ መርሃ ግብር (project work schedule) እንዲሁም ባቀረበው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ (conformation letter) አሸናፊነቱ በተገለፀ በ5 ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 25 ፐርሰንት የማስያዝ ግዴታ እንዳለበት ከወዲሁ ማወቅ አለባቸው።

11. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፈ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ የሂሳብ ስሌት ከተሰራ በኋላ የተደረገበት ልዩነት እስከ 2.5 ፐርሰንት ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከ2.5 ፐርሰንት በላይ ልዩነት ካመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

12. ተጫራቾች ሶስት እና ከዛ በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ የሂሳብ ስሌት ከተሰራ በኋላ የተደረገበት ልዩነት እስከ አንድ ፐርሰንት ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ደ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት ሰነዱን ብር 300/ሶስት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።

15. የመጫረቻ ሰነዱ ላይ በአንድ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

16. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 033 461 0335 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-24 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dehana Woreda FEDB
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T10:22:46.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders