የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለመስክ ሥራ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- ኢፕድ 024/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለመስክ ሥራ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዉድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል መሆኑና ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዚጋጀው በአቅርበት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚውል ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ቢድቦንድ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1ኛ ፎቅ በአቅርቦት መምርያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 156 9869
ኢ ሜይል procurement@press.et
አድራሻ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-06-19 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Jun 04, 2026
- Posted at: 2026-06-04T08:04:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.