የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የመስክ ሥራ፣ የሰራተኞች ትራንስፖርት እና የፕሮጀክቶች እንቅስቃሴ ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ ሚኒባስ፣ ፒክአፕ እና ስቴሽን ዋጎን ተሽከርካሪዎችን ኪራይ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/PNCS-S32/2018

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በስሩ ላሉ ፕሮጀክቶች የመስክ ሥራ፣ የሰራተኞች ትራንስፖርት እና የፕሮጀክቶች እንቅስቃሴ ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ ሚኒባስ፣ ፒክአፕ እና ስቴሽን ዋጎን ተሽከርካሪዎችን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ከታች የተጠቀሱትን ሰነዶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፤ የአቅራቢነት ዝርዝር የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ክሊራንስ እና የመልካም አፈፃፀም የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ጥሬ ገንዘብ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ዋና መምሪያ በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
  3. የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡት ሰነድ ፋይናንሺያል ኦሪጅናልና ኮፒ ሲሆን ለየብቻ በማሸግ በፖስታው ላይ ዝርዝር መረጃ (ዋና እና ኮፒ የሚል፣ የአጫራች ድርጅት ስምና አድራሻ በመፃፍ ወደተዘጋጀው ሳጥን አስመዝግበው ማስገባት ይጠበቅባዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራች 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለበት።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። ዘግይቶ የቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባነት የላቸውም።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀን ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ ዋና መምሪያ ይከፈታል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ ቢሮ

አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 011 896-2991 /011 872 2947

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-16 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC)
  • Buyer TIN: 0048380057
  • Buyer address: ECWC Building at Gurd Shola, In front of Andinet International School
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 04, 2026
  • Posted at: 2026-06-04T08:25:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders