የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለሚያለማው አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ክሎት 051/2018 እስከ ሎት 148/2018 ድረስ ያሉት 98 ሎቶች ለማሰራት ያስፈለገ በመሆነ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት በዘርፉ ከተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለሚያለማው አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ክሎት 051/2018 እስከ ሎት 148/2018 ድረስ ያሉት 98 ሎቶች ለማሰራት ያስፈለገ በመሆነ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት በዘርፉ ከተደራጁ ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት:ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራት መወዳደር ይችላሉ፡-

በአረንጓዴ ልማት ተደራጅቶ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት፤

1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፣የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

4. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ሃያ/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 400(አራት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።

6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

8. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ 1 ካለና የሥራዉ አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም። ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

9. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከአምስት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

10. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ አሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

11. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች (ከ20–30%) ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሰንት በታች መውረድ የለበትም።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046-220-9963 / 046-212-1334

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መም


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: Jun 05, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders