በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው እቃዎች በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ሐራጅ ጨረታ ቁጥር 19/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው
- ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ)፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- poly(ethylene terephthalate) plastic cas(ጥሬ ፕላቲክ) ፣
- ኮስሞቲክስ fabric rope(አልባሳት) ፣
- የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣
- ምግብ ነክ (ድብልቅ ስንዴና ገብስ)፣
- አዳዲስ አልባሳት ጫማዎች) እና አዳዲስ አልባሳት
በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን:
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው ፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖሩም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆነ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ሥር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
4. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የጨረታው አይነት |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን |
ጨረታው የሚከሄድበት ቀን |
ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት |
ስልክ ቁጥር
|
|
1 |
ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
2 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
3 |
POLY (ETHYLENE TEREPHTHALATE) PLASTIC CAS (ጥሬ ፕላስቲክ ) |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925
|
|
4 |
ኮስሞቲክስ |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
5 |
fabric rope(አልባሳት) |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
6 |
የኮንስትራክሽን ማቴሪያል |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
7 |
አዳዲስ አልባሳት |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
8 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
9 |
ምግብ ነክ (ድብልቅ ስንዴና ገብስ) |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
|
10 |
አዳዲስ አልባሳት (ጫማዎች) |
ሐራጅ |
28/09/2018 |
03/10/2018 |
4:00 |
8:00 |
0221118429/02 22118925 |
4. በጨረታው ሽያጭ የዕቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
5. በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤
- ለምድብ 01, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 77,800.00፣
- ለምድብ 02, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 12,900.00፣
- ለምድብ 03 ኤሌክትሮኒክስ ብር 211,200.00፣
- ለምድብ 04,ኤሌክትሮኒክስ ብር 72,000.00 ፣
- ለምድብ 05, ኤሌክትሮኒክስ ብር 67,500.00
- ለምድብ 06, poly(ethylene terephtalate) plastic cas(ጥሬ ፕላቲክ) ብር 67,600.00
- ለምድብ 07, ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩ) ብር 33,300.00 ፣
- ለምድብ 08, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 191,500.00 ፣
- ለምድብ 9, ኮስሞቲክስ ብር 110,200.00 ፣
- ለምድብ 10, ኮስሞቲክስ ብር 114,000.00 ፣
- ለምድብ 11, ኮስሞቲክስ ብር 406,400.00 ፣
- ለምድብ 12 fabric rope ብር 69,100.00 ፣
- ለምድብ 13, ኤሌክትሮኒክስ ብር 47,000.00 ፣
- ለምድብ 14, ኮስሞቲክስ ብር 116,000.00 ፣
- ለምድብ 15, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ብር 213,500.00፣
- ለምድብ 16, አዳዲስ አልባሳት ብር 14,800.00፣
- ለምድብ 17, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) 5,000.00 እና
- ለምድብ 18, አዳዲስ አልባሳት ብር 192 800.00፣
- ለምድብ 19, ኤሌክትሮኒክስ ብር 240, 800.00፣
- ለምድብ 20, ኮስሞቲክስ ብር 849,300.00 እና
- ለምድብ 21, ምግብ ነክ( ድብልቅ ገብስና ስንዴ) ብር 320,200.00 ፣
- ለምድብ 22 ኤሌክትሮኒክስ ብር 219,200.00፣
- ለምድብ 23 ኮስሞቲክስ ብር 18,300.00 ፣
- ለምድብ 24 ኮስሞቲክስ ብር 1,800.00፣
- ለምድብ 25 አዳዲስ አልባሳት(ጫማዎች) ብር 2,673,300.00 እና
- ለምድብ 26 ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 203,400.00 (Customs Commission Adama Branch)
ስም ብቻ ሲፒኦ በማሠራት ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
6. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን ዕቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማየት እና መጫረት ይቻላል
7. በሐራጅ ጨረታ የዕቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሦሰት የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
1ዐ. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ ዕቃ መጠየቅ አይችሉም።
11. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟላ ተጫራች ቢያሸንፍ : ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ እና ዕቃው በድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናስታውቃለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11- 5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-10
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-10 14:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jun 05, 2026
- Posted at: 2026-06-05T08:19:51.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.