የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የ Sanitary Material አቅርቦት ግዥን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/SM/57/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የ Sanitary Material አቅርቦት ግዥን አስመልክቶ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

.

የስራ ዝርዝር

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

Supply Sanitary Material

DCE/SM/57/2026

12/10/2018 .ምከጠዋቱ 415

12/10/2018 . ከጠዋቱ 4:30

ስለሆነም፦

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ….ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  4.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ።
  5.  ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 12/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6.  ጨረታው ሰኔ 12/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
  7.  አንድ ተጫራች ለአንድ ዕቃ መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል/ብራንድ/ ብቻ ነው ፤ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡
  8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር ቁጥር 0114-40-34-34/33

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 WWW.dce-et.com /Email: Info@dce-et.com

ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-19
  • Bid closing time: 10:15
  • Bid opening: 2026-06-19 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 05, 2026
  • Posted at: 2026-06-05T08:42:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders