ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የDesktop Computer and Related Accessories ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EAC 034/2018
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የDesktop Computer and Related Accessories ግዥን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 –6፡30 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ” ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
- አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የ Desktop Computer and Related Accessories ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.p.O/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 የሚከፈት ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 መጠቀም ይችላሉ።
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-06-15 10:45
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T08:55:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.