የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓም በመደበኛ ካፒታል በጀት የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ለመፍጠር ሁለት አዳዲስ የሶፍትዌር ሲስተም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 010

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓም በመደበኛ ካፒታል በጀት የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ለመፍጠር ሁለት አዳዲስ የሶፍትዌር ሲስተም ማለትም TMlS/Teachers Management information System/ እና LMS /Learing Management System/ ሶፍትዌር ለመግዛትና ወደ ሥራ ለመግባት በመፈለጉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይንም መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

መስፈርት፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣አስተማማኝ ዋስትና መስጠት የሚችል፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንዳንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6.መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-771 0688 መደወል ይችላሉ ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Publishing entity: Central Ethiopia Regional State Education Office
  • Bid bond: ብር 100,000
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 07, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders