በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለታጠቅ እና ለሙገር ጥበቃ፣ ፅዳት፣ መስተንግዶ የጉልበት እና ለተለያዩ ሥራዎች የሰው ሀይል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል

Description

የሀገር ውስጥ የጨረታ ቁጥር

ሙሲፋ/10/2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለታጠቅ እና ለሙገር ጥበቃ ፅዳት መስተንግዶ የጉልበት እና ለተለያዩ ሥራዎች የሰው ሀይል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል። 

ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018ዓ/ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት (ገርጂ መንገድ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ህንፃ) ከሚገኘው የግብ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖረሽን ሀገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.PO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በገዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም.ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በገዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ስልክ፡-011 442 0216

ፋክስ፡-011 442 0688

አዲስ አበባ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-06-30 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mugher Cement Factory
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 575.00 ብር
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T09:11:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders