የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ሁለተኛ ዙር የሀራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ከወ/ሪት ጽዮን ጌታቸው ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና 807/2005 መሰረት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተቁ |
የንብረቱ ዝርዝር
|
ብዛት በቁጥር |
የጨረታው መነሻ ዋጋ |
የንብረቱ ሁኔታ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Baking Rotary Oven with Burner Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF200,Origin: Turkey |
1 |
10,370,520.53 |
አዲስ
|
ሀምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እሰከ 6:00 ሰዓት
|
|
2 |
Mixer Brand: PORLANMAZ, Model: PMSP120,Origin: Turkey |
1 |
|||
|
3 |
Dough Divider -Brand: PORLANMAZ, Origin: Turkey |
1 |
|||
|
4 |
Dough Moulder Machine - Brand: PORLANMAZ, Model: PMD350 Origin: Turkey |
1 |
|||
|
5 |
Proofer with Steam Generator - Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF204,Origin: Turkey |
1 |
|||
|
Steamer -Model: _ PMCU10,Origin: Turkey |
|
||||
|
6 |
Trolley with 14trays - Brand: PORLANMAZ - Number of pans per trolley - 16 material stainless steel |
4 |
|||
|
7 |
Bread Slicer Brand: PORLANMAZ Model: PMBS500, Origin: Turkey |
1 |
|||
|
8 |
Sound Proof Generator - Brand: AKSA, Model: AP33, Rated power: 33KVA |
1 |
የሀራጁ መመሪያ
1. ንብረቱን መግዛት መከራየት የሚፈልግ ተጫራች የሀራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 2,074,104,11 ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ብር ከ11/100 ሳንቲም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ በሀራጁ መሳተፍ ይችላል። ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ከንብረቱ የመሸጫ ሂሳብ ላይ ተጫራቹ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚቀነስ ይሆናል፤
2 ንብረቱ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሃዋሳ ከተማ፡ መናኻሪያ ከ ከተማ፣ ጉዊ ቀበሌ፣ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ይገኛል።
3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
4. ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በካሸ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
5. የሐራጁ አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የሀራጁ አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ - ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ለሀራጁ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
6. ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መሰፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሸነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያሰያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንክ ገቢ ይደረጋል።
7. የካፒታል ዕቃውን ካለበት መጋዘን ወደ ሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ የጉዞ አንሹራንስ፣ የመትከያ፣ ስራ የማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ተከራይ ይሸፍናል።
8. ሀራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ይካሄዳል።
9. ሰለ ንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
10. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪከት ጋር አሰቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሀራጁ አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-07-10
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 20%
- Published: Jun 07, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.