በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሰንዳፋ ሶላር ፋብሪካ የአጥር ግንባታ በኤጋ ቆርቆሮ ግዥ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል
Description
ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሰንዳፋ ሶላር ፋብሪካ የአጥር ግንባታ በኤጋ ቆርቆሮ ግዥ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት
4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለበት
5. ተጫራቾች በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት።
7. ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢክፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ
9. ተጫራቾች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሁኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
11. ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
12, የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
13. አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ለጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 (GC -5) በላይ ወይም ለህንጻ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 4(BC-4) በላይ መሆን አለባቸው ለዚህም ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት አስፈላጊ ነው።
14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ይዘጋል። በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
15. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።
16. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልከ: +251 92 495 5389፣ +251 91 016 2733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፖወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-06-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30
- Bid opening: 2026-06-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Engineering Group Power Equipment Manufacturing Industry
- Buyer address: ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
- Bid bond: 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር)
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T09:33:51.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.