ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የፅዳት አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለቢሮ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ፓርኪንግ እና ፕላዛ ላይ የፅዳት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የፅዳት አገልግሎት ግዥ

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 023/2018

ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የፅዳት አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለቢሮ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ፓርኪንግ እና ፕላዛ ላይ የፅዳት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል።

1. በዘርፉ የተሰማራና ከድርጅታችን ጋር በማንኛውም ሥራ ውል ፈጽሞ እየሰራ ያልሆነ፣

2. ከማንኛውም ዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆነ ድርጅት፣

3. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ከሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ለ8 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 9ኛው ቀን ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት 8፡35 ሰዓት የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ብር 500/አምስት መቶ/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለየብቻ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።

8. ይህ ጨረታ በድርጅቱ የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

9. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 3 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10% የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

10.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን መስቀል አደባባይ በሚገኘው የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ማግኘት ይችላሉ።

12. ማሳሰቢያ፦የፋይናንስ ውድድሩ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለየብቻ በሚቀርብ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በሚሞሉት መሰረት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 011 515 1693 መጠየቅ ይችላሉ።

ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-06-15 14:35
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Exhibition Center & Market Development Enterprise
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T10:31:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders