ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የድራፍት ማሽን በርሜል መጋዘንን ሼድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ቁጥር HBSC/01/02428/26

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ.

የድራፍት ማሽን በርሜል መጋዘን ሼድ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ HBSCKESHADE/01/0001/26

የድራፍት ማሽን በርሜል መጋዘን ሼድ ጨረታ ማስታወቂያ

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የድራፍት ማሽን በርሜል መጋዘንን ሼድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

2. በደረጃው ቢሲ-5 ጂሲ 5 እና ከዚህ በላይ ፍቃድ ያላቸው

3. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፤

5. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው

6. ተጫራቾች ከላይ የተገለፁት መስፈርት አሟልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በአካዉንት ቁጥር 1000004335299 በመክፈል የገባበትን ስሊፐ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ

ሀ) ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ አሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የጨረታ ማስከበሪያዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሽግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት

ለ) ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሽግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ /ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

8. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሐበሻ ቢራ አ.ማ ስም እና ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።

9. ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፤

10. የጨረታው ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-22 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Habesha Breweries S.C.
  • Buyer address: ቦሌ ከአዲስ የልብ ህክምና ጎን/ካርጎ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T11:54:02.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders