ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የግንባታ ማህበራትን አወዳድሮ የተለያዩ ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን በአምስት ወረዳዎች በሚገኙ 15 (አስራ አምስት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 4 (አራት) ጤና ተቋማት፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን በምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ በሚገኙ 4 (አራት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 2 (ሁለት) ጤና ተቋማት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በህመር እና በበና ጸማይ ወረዳዎች በሚገኙ 6 (ስድስት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 4 (አራት) ጤና ተቋማት እንዲሁም በሲዳማ ክልል በሃቤላ ወረዳ በሃቤላ ሊንዳ
1ኛ ደረጃ ት/ቤት በድምሩ በ 26 ት/ቤቶች እና በ 10 ጤና ተቋማት የዝናብ ዉሃ መሰብሰቢያና የፊት መታጠቢያ ለመገንባት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የግንባታ ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸዉን እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፣
2. የዉሃ ስራ ደረጃ 8 ወይም 9 ያላቸዉ፣ ወይም የግንባታ ፈቃድ ደረጃ 8 ያላቸዉ፣
3. ህጋዊ የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ከዞን ዉሃ ወይም ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ወይም ከዚህ በፊት ከሰሩበት ዞን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ማህበራቱ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥ የተዘረዘሩትን የግንባታ ቁሳቁስ በግዥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
6. ተጫራቾች የጨረታዉን ዶክመንት ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ፣ በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ቢሮ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብር 200.00 በኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የህብረት ባንክ አካዉንት ቁጥር 1131810577203010 በማስገባትና ደረሰኝ በማቅረብ መዉሰድ ይችላሉ፣
7. ተጫራቾች ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን እና የግንባታ ቁሳቁስ እና የጉልበት ጥቅል ዋጋ በወሰዱት የጨረታ ሠነድ ላይ ሞልተዉ ኦሪጂናል፣ ኮፒ 1 አና ኮፒ 2 ብለዉ በመጻፍና በአንድ ኢንቨሎፕ ዉስጥ በማድረግ በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በወሰዱበት የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣
8. አንድ ማህበር ከ7 (ሰባት) የግንባታ ቦታዎች በላይ መወዳደር አይችልም፣ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ት/ቤቶች እና ጤና ተቋማት ስም በፖስታዉ ላይ በግልጽ መጥቀስ አለባቸዉ፣ እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት የግንባታ ቁሳቁስ እና የጉልበት ዝርዝር ዋጋ የወቅቱን ገበያ ግምት ዉስጥ ያስገባ መሆን አለበት፣
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የ 5000.00 (አምስት ሽህ) ብር CPO (ለአንድ ት/ቤት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
10.ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፣
11.ከዚህ በፊት በአፈጻጸማቸዉ ማስጠንቀቂያ የተጻፈባቸዉ ማህበራት መወዳደር አይችሉም::
ማሳሰቢያ፡ የጨረታ ሰነዱን ለመዉሰድ ሲመጡ የማህበሩን የታደሰ ፈቃድ ኮፒ ይዘዉ ይቅረቡ፣ የት/ቤቶቹን መረጃ ከአባሪዉ ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡ በ 011 662 0996 ወይም ለሚዛን በ09 17 25 94 24/ 09 11 24 95 53 ለምዕራብ ባዳዋቾ 09 17 82 25 78 ፣ ለደቡብ ኦሞ በ09 79 81 04 89/ 09 17 82 25 78 ለሲዳማ በ09 73 99 56 21 ይደዉሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-22 14:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Orbis International Ethiopia (OlE)
- Buyer address: Yeka Sub-City, Haile Gebreselassie avenue,Rebecca Building, 3rd Floor,
- Bid bond: 5000.00 ብር ለአንድ ት/ቤት
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T11:57:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.