ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ ማህበር የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ከሚሰጡ ድርጅቶች አወዳድሮ ለማግኘት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር: EBG/002/26
ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ ማህበር እ.ኤ.አ ከጁላይ 1. 2026 ዓ.ም እስከ ጁን 30, 2027 ዓ.ም ድረስ ላለው የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ከሚሰጡ ድርጅቶች አወዳድሮ ለማግኘት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት፡-
- የህይወት ኢንሹራስ ግሩፕ ተርም እና ህክምና
- የተሽከርካሪ
- የህንፃ ንብረት ቃጠሎና ስርቆት
- የገንዘብ እምነት ማጉደል
- ሞተር ትሬድ ዋስትና ኢንሹራንስ
ስለዚህ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በሚከተሉት መስፈርቶች መሠረት ጨረታውን መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ከኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ የሀገር ውስጥ ግዥ ቢሮ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ ክፍያ በመክፈል ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የብቃት ማረጋገጫ እና 5,000.00 ብር (አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ዋስትና (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን በሁለት የተለያዩ የታሸጉና በሰም የታተመ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
- ሌሎች ሁሉም ከዚህ ግልጽ ጨረታ ጋር የተያያዙ መረጃዎች ከTOR ጋር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛሉ፤ ተጫራቾች በጥብቅ መከተል አለባቸው።
- ጨረታው እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት መግባት አለበት።
- ጨረታው በ EBG 2ኛ ፎቅ የኮንፈረንስ ክፍል በተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው ፊት ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሠዐት ይከፈታል።
- በሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱ መመሪያዎችና መስፈርቶች ካልተከተሉ ተጫራቹ ከውድድሩ ይወገዳል።
- ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ተጫራቾች በሚከተለው አድራሻ ሊያገኙ ይችላሉ።
አድራሻ፡
ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማ ዋና መስሪያ ቤት
አዲስ አበባ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 6፣ ቤት ቁጥር 402
ስልክ፡ +251114406218 / +251114424955
ፖ.ሳ.ቁ፡ 8964
Tender details
- Deadline: 2026-06-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-17 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Equatorial Business Group P.L.C
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T14:48:41.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.