የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በኢቶል (ETOL) በተመደበ በጀት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ 19 ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፡ 19 ፕሪንተሮች እና 19 ቴሌቪዝኖች ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EB/EMAS/025/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በኢቶል (ETOL) በተመደበ በጀት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ 19 ዴስክቶፕ ከምፒውተሮች፡ 19 ፕሪንተሮች እና 19 ቴሌቪዝኖች ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊና በዘርፉ አግባብነት ያለው የንድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ዕቃዎች አይነትና ቴክኒካል የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 15 ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 9 ባሉ ንዑሳ ቁጥሮች ላይ በዝርዝር በተቀመጠው መሠረት ይሆናል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ግብዓት ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ ማስገባት የሚቻለው እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል።
9. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሑድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 5654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሑድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-23 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሑድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Region Education Bureau
- Bid document price: 600.00 ብር
- Published: Jun 08, 2026
- Posted at: 2026-06-09T08:09:00.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.