የፕላስቲክ ማምረቻ ማሽኖች እና ባጃጅ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የፍባለመበት እነ ዶር አበበ ሐረገወይን እና በፍ ባለዕዳ አንያ ፕላስቲከስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 212218 በቀን 22/5/2018 ዓ.ም እና 212218 በቀን 13/06/208 ዓ.ም እና 215038 መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወ/07 የቤ/ቁ 1562 ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ የፕላስቲክ ማምረቻ ማሽኖች የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,976,700.00 (አንድ ሚሊዬን ዘጠኝ መቶ ሰባ ስድስት ሺ ሰባት መቶ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆነ ታውቆ በሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወ/07 የቤ/ቁ 1562 ውስጥ የሚገኝ አንድ ያገለገለ ሞዴል ባጃጅ Bajaj 100 ሞተር ሳይክል የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት /ስም C.RO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 15:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-26 15:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 08, 2026
- Posted at: 2026-06-09T08:15:22.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.